Featured

የታሸገ ውሃ አምራቾች በሰማያዊ ፕላስቲክ ጠርሙስ ማምረት አቆሙ

የአገር ውስጥ የታሸገ ውሃ አምራቾች ሲያመርቱበት የቆየውን ሰማያዊ የፕላስቲክ ጠርሙስ በመተው ውሃን በነጭ (ቀልም አልባ) ፕላስቲክ ጠርሙስ ማሸግ ጀመሩ፡፡ለረጅም አመታት አምራቾቹ ሰማያዊ ቀለም ባላቸው የፕላስቲክ ጠርሙሶች ሲያሽጉ የነበረ ቢሆንም የምግብና መጠጥ ኢንዱትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ባካሄደው ጥናት የፕላስቲክ ጠርሙስ ማቅለሚያ አካባቢ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ መልሶ ለግብአትነት ለመጠቀም አመቺ ባለመሆኑ እና አላስፈላጊ የውጭ ምንዛሬ ወጪን የሚያስከትል በመሆኑ የጠርሙስ ማቅለሚያ ማስተርባች ጥቅም ላይ እንዳይውል ተወስኗል፡፡
 
የኢትዮጵያ መጠጦች አምራች ኢንዱስትሪ ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርድ ለኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደተናገሩት ጥናቱ ለአንድ አመት ያህል ከተካሄደ በኋላ ፕላስቲክ ጠርሙስ ማቅለሚያ መነሳቱ እና በነጭ ጠርሙስ ውሃ ማሸጉ በአካባቢ ላይ ያለውን ተፅዕኖ የሚቀንስ እና የውጭ ምንዛሬን ለማዳን የሚረዳ በመሆኑ ውሳኔው ተላልፏል፡፡
 
በመሆኑም የታሸገ ውሃ አምራቾች ውሳኔውን ተቀብለው ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በነጭ (ቀልም አልባ) ፕላስቲክ ጠርሙሶች ማምረት መጀመራቸውን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡
ውሃ አምራቾች በተለያዩ ግብአቶች እጥረት እና ዋጋ መናር መቸገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
 
(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)

Visitor Counter

Today 10

Yesterday 363

Week 1191

Month 10166

All 931380

Events - Calendar

December 2024
S M T W T F S
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30 31

Contact Us

Office Phone: +251-116 663344

Mobile: +251-953855505

Fax: +251-116 663650

Email: info@ebmia.org

Website: www.ebmia.org

Addis Ababa, Ethiopia