የታሸገ ውሃ አምራቾች ቀለም አልባ ፕላስቲክን በመጠቀማቸው በአመት 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪን እንደሚያስቀር ተገለፀ
Featured

የታሸገ ውሃ አምራቾች ቀለም አልባ ፕላስቲክን በመጠቀማቸው በአመት 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪን እንደሚያስቀር ተገለፀ

የታሸጉ ውሃ አምራቾች ሲጠቀሙበት የነበረውን የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙስ ማቅለሚያ (ማስተርባችን) በማስቀረቱ አምራቾቹ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት ሲጠቀሙበት የነበረውን በአመት ውስጥ እስከ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጪን እንደሚያስቀር ይፋ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ መጠጦች አምራች ኢንዱስትሪ ማኅበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌትነት በላይ ሐሙስ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የፕላስቲክ ጠርሙስ መሆን ፕላስቲክን መልሶ በመጠቀም (Recycle) በማድረግ እስከ 25 በመቶ የሚሆነውን ከፕሪፎርሙ (ጥሬ ዕቃው) ጋር በመቀላቀል መልሶ መጠቀም የሚቻል መሆኑን ለአምራቹ እድል ፈጥሯል፡፡
የፕላስቲክ ጠርሙሱ ተፈጭቶ እና ተቀነባብሮ ወደ ውጭ ሃገር በሚላክበት ወቅት ቀድሞ ከነበረው (ማስተርባች በነበረበት ወቅት) በ1 አመት ውስጥ በአማካኝ በአንድ ቶን እስከ 15 ዶላር ተጨማሪ ገቢ እንዲገኝ ማገዙንም ኢንጅነር ጌትነት ተናግረዋል፡፡

ማስተርባቹ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ሲያባብስ የነበረ ከመሆኑም ባሻገር ሃገር ውስጥ መልሶ ለመጠቀም (Recycling) ለማድረግ አመቺ አለመሆኑ፣ የማምረቻ ወጪን የሚጨምር መሆኑ፣ አካባቢን በይበልጥ ይበክል የነበረ መሆኑ እንዲሁም የአስገዳጅ የጥራት ደረጃ ላይ ያልተካተተ መሆኑም ሲነገር ቆይቷል፡፡
የታሸገ ውኃ አምራቾች በተለይም በጥሬ ዕቃ እጥረት ለማምረት ሲቸገሩ መቆየታቸውንና ለዚህም እንደ መፍትሔ ከተወሰዱት ጉዳዮች መካከል ተጨማሪ ግብዓቶችን መጠቀም ማቆም መሆኑን የኢትዮጵያ ውኃ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አሸናፊ መርድ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)

Visitor Counter

Today 368

Yesterday 421

Week 2978

Month 2520

All 985480

Events - Calendar

October 2024
S M T W T F S
1 2 3 4 5
6 7 8 9 10 11 12
13 14 15 16 17 18 19
20 21 22 23 24 25 26
27 28 29 30 31

Contact Us

Office Phone: +251-116 663344

Mobile: +251-953855505

Fax: +251-116 663650

Email: info@ebmia.org

Website: www.ebmia.org

Addis Ababa, Ethiopia