የማህበሩ ምስረታ በምግብ መጠጥና ፋርማስቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቱዩት የመሰብሰብያ አዳራሽ ሲከናወን የተገኙት የመጠጥ ፕሮሰሲንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ሰለሞን የዘርፍ ማህበሩ መመስረት በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ጉልህ አስተዋኦ እንዳለው ተረድተው ማህበሩ እንዲመሰረት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ አምራቾች ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰክቶራል ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ታሪኩ ዶቸ በበኩላቸው የማህበሩ መመስረት ለአምራቹም ሆነ ለመንግስት ከፍተኛ ጥቅም አለው ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም የዘርፍና የሙያ ማህበራትና ምክርቤት አደረጃጀትና ድጋፍ አሰጣጥን በተመለከተ መመርያ አውጥቶ አምራቾች በማህበር እንዲደራጁ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል ፡፡