በኢትዮጵያ ውሃ እየባከነ ነው ተባለ።

ዛሬ ላይ የከርሰ ምድር ውሃ ለማግኘት 200 ሜትር ድረስ እንደሚቆፈር ተሰምቷል። ይህም ውሃ እየጠፋ እንደሆነ ምልክት ነው ተብሏል። የከርሰ ምድር ውሃ እንዳይባክን በቁጠባና በኃላፊነት ለማሥተዳደር ፖሊሲ ያስፈልጋል ተብሏል።

የታሸገ የውሃ አምራች ድርጅቶች ከአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች ሥራዎች ጋር በተገናኘ አንድ ላይ ለመሥራት መስማማታቸው ተሰምቷል። የታሸገ ውሃ እና የለስላሳ መጠጥ አምራች ድርጅቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አቀናባሪ እና ጨማቂዎች፣ እንዲሁም ሌሎችም አንድ ላይ ለመሥራት ሕብረት ፈጥረዋል ተብሏል።

ሕብረቱ የሐገሪቱ የከርሰ ምድር ውሃ እንዳይባክን ከፖሊሲ አውጭዎች እና ከሚመለከታቸው ጋር ፕሮጀክት ቀርፆ ይሠራል ተብሏል።ፕሮጀክቱ የውሃ አካውንቲንግ ጥናት ወይም የኢንዱስትሪዎችን የውሃ አጠቃቀም መረጃ ለመሰብሰብ ያግዛል ተብሏል።

በሕብረቱ ዎተር ኤይድ፣ የዓለም ባንክ፣ ኮካኮላ ኩባንያ፣ የታሸገ ውሃ እና የፍራፍሬ ጨማቂዎች ማኅበር፣ እንዲሁም ሌሎች በጎ ፈቃደኞች ተሰባስበዋል። ወደፊትም ከመንግሥት የፖሊሲ ድጋፍ ለማግኘት በብርቱ ለመሥራት መታሰቡን ሰምተናል።ሕብረቱን ለማቋቋም 135 ሺህ ዶላር በጀት ለመመደብ ተወጥኗል።

ከ20 ዓመት በኋላ የዓለም ሕዝብ ቁጥር በ3 እጥፍ ሊጨምር ይችላል። ይህን ተከትሎ ዓለምን ድርቅ ሊመታት እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።ስለዚህ ውሃ እንዳይባክን በሀገር ቤት ፖሊሲ ያስፈልጋል ተብሏል።ዓለም 3/4ተኛው ክፍሏ ውሃ ቢኾንም፣ ለሰው ልጅ መዋል የሚችለው ግን 5 በመቶ ብቻ እንደሆነ ይታወቃል።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የውሃ እጥረት ለዓለም ስጋት ከሚሆኑ ጉዳዮች ሦስተኛው እንደሚኾን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

ፍላጎት እና አቅርቦቱ ላይመጣጠን እንደሚችልም ተሰምቷል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

Visitor Counter

Today 367

Yesterday 421

Week 2977

Month 2519

All 985479

Events - Calendar

October 2024
S M T W T F S
1 2 3 4 5
6 7 8 9 10 11 12
13 14 15 16 17 18 19
20 21 22 23 24 25 26
27 28 29 30 31

Contact Us

Office Phone: +251-116 663344

Mobile: +251-953855505

Fax: +251-116 663650

Email: info@ebmia.org

Website: www.ebmia.org

Addis Ababa, Ethiopia